በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቆች እና የፈርኒቸር ውጤቶች፣ እንዲሁም የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃ አቅርቦት ግዥን በሀገር አቀፍ ግልዕ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የቋሚና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ግዥ ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቆች እና የፈርኒቸር ውጤቶች፣ እንዲሁም የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃ አቅርቦት ግዥን በሀገር አቀፍ ግልዕ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡
- ከሚወዳደሩት አቅርቦት ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸዉ ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer Identification Number) ያላቸው።
- በግዥ አፈጻጸም መመሪያው የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ዉጭ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን እቃ እና አገልግሎት አይነት ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /ምድብ/ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ/ በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ምድብ ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናዉን የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስራ አምስተኛዉ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ርቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታዉ በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ እንስቶ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጥዋቱ 3፡30 ይከፈታል፣ ሆኖም ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ከመንግሰት የስራ ቀን ዉጭ ከሆነ በተመሣሣይ ሰአት በሚቀጥለዉ የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል፡
- መምሪያዉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ይህም ሲባል ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0334401230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
