Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline27 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-27 00:00:00
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant , Machinery , Metals And Metal Working , Vehicle , Used Items

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር /EEP/DS/03/18

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

ሎት 1 በታላቁ ህዳሴ ፕሮጀክት የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ፣ ማሽነሪ እና ተሽከርካሪዎች

ሎት 2 በመካከለኛ ሪጅኖች (አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ኃ/ማ/ጣቢያዎች) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 3 ደቡብ 1እና2 ሪጅን (ሶዶ 1፣ አርባ ምንጭ፣ ሳውላ፣ ሃላባ፣ ሀዋሳ) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 4 በሰ/ምስራቅ 1 ሪጅን (ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ 1እና2፣ ጋሸና) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 5 ምስራቅ 2 ሪጅን (ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ፊቅ፣ ደገሃቡር) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 6 ምዕራብ ሪጅን (ነቀምት፣ ጌዶ፣ ፊንጫ፣ መንዲ፣ ሻምቡ፣ ጊምቢ፣ አሶሳ፣ ደዴሳ፣ ባኮ፣ ጊዳሚ) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 7 ደቡብ ምዕራብ ሪጅን (ጂማ 1እና 2፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ በደሌ፣ አጋሮ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ግልገል ጊቤ) ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 8 ተከዜ ኃይል (ትግራይ ክልል) ማመንጫ ጣቢያ የሚገኙትን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረቶች፣ቁርጥራጭና ስክራፕ

ሎት 9 ከውሃ ጋር የተደባለቀ ነዳጅ (ዋና መ/ቤት ኮተቤ ግቢ)

ሎት 10 ከተሽከርካሪ የተቀየረ የተቃጠለ ዘይት (ዋና መ/ቤት ኮተቤ ግቢ)

ሎት 11 የትራንስፎርመር ዘይት (በአዲሰ አበባ እና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ባሉ ቦታዎቸ)

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተወዳዳሪዎች ከሎት አንድ እስከ ሎት ስምንት ላይ ለመሳተፍ በብረት አቅላጭ ድርጅትነት የተሰማሩ መሆን ያለባቸው ሲሆን፤ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ከ03/03/2018 እስከ 18/03/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋት 3፡00 ድረስ ይካሄዳል። ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡
  10. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፡፡
  11. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

 

Save Tender