Tender Detail

Tender Details

  • Company የሞጣ ከተማ መጠጥና ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ሞጣ ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058 661 1971
  • Website
  • Deadline25 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-11-26 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing , Finance

የሞጣ ከተማ የመጠጥ ውኃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የ4(አራት) ዓመት ማለትም 2014፤ 2015፤ 2016 እና 2017 ዓ/ም በጀት አመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።

የሞጣ ከተማ መጠጥና ውሃ አገልግሎት ድርጅት


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኦዲት/ሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሞጣ ከተማ የመጠጥ ውኃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የ4(አራት) ዓመት ማለትም 2014፤ 2015፤ 2016 እና 2017 ዓ/ም በጀት አመት ሂሣብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላሉ።

  1. መ/ቤቱን/ ድርጅቱን) ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፣
  2. ለሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ማስያዝ ይኖርበታል
  3. የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃድን ያደሰ፣ ፍቃዱን ያሳደሰ፣
  4. የሂሣብ ምርመራው ኦዲቱ በሞጣ ከተማ የሞጣ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሣተፍ
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በግልፅ በአየር ላይ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ዘወትር የሥራ ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ከቢሮ ቁጥር 12 በመግዛት መጫረት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን /ታክሱን ጨምሮ/ በጨረታ መመሪያው መሠረት በመሙላት በተራ ቁጥር 12 በተገለጸው የሥራ ቀን በታሽገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናሉን ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 12 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን “የቴክኒክ ማወዳዳሪያ ሠነድ” እና የዋጋ ማወዳዳሪያ ሠነድ እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያውን ጨምሮ በመለየት በኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሠነድ ላይ ሠርዝ ድልዝ መኖር የለበትም /ካለም ስለእርማቱ በፈርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
  9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱን በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን አንሰቶ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ የዋጋውን 10% በዋስትና ላይ የተመሰረተ ወይም CPO በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል።
  10. አሸናፊው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅደመ ሁኔታውን አሟልቶ በመቅረብ ውል ካልያዘ ጨረታውን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመ/ቤቱ / ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
  11. የጨረታ ሠነድ ማስገቢያው የጊዜ ገደብ ከማለቁ በፊት በማናቸውም ጊዜ መ/ቤቱ /ድርጅቱ ጨረታውን በተመለከተ ማስተካከያ ካለው ማስተካከል ይችላል። ሆኖም ማስተካከያውን በጽሁፍ ለሁሉም ተጫራቾች ይገልፃል።
  12. አጠቃላይ የኢትዩጵያ መንግስት የሂሣብ አያያዝ ስርዓትና የኦዲት ደረጃዎችን ተከትሎ መሠራት የሚኖርበት ሆኖ የጥሬ ገንዘብ ሂሣብ፣ የገቢ ሂሣብ፣ የወጪ ሂሣብ፣ የተሰብሳቢ እና ተከፋይ ሂሣቦች፣ የንብረት ሂሣቦች፣ የሰው ኃይል መረጃዎች እንዲሁም ሌሎች የተቋሙ መመሪያዎችና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎች ማየትና መመርመር የሥራው አካል ነው። በመጨረሻም በሂሣብ ምርመራው ውጤት መሠረት በሂሣብ ሪፖርት ላይ ሙያዊ የኦዲት አስተያየት /Audit Opinion/ መስጠት ይጠበቅበታል።
  13. ጨረታው ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሽጋል። በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ የቴክኒካል ሠነድ ብቻ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው / በተገኙበት በዕለቱ ይከፈታል። በቴክኒካል ውጤት 70% እና በላይ ያገኙ ተጫራቾች ብቻ ለዋጋ ውድድር እንዲገኙ ጥሪ ይደረግላቸዋል። በቴክኒክ መስፈርቱ ከ70% በታች ያገኙ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማወዳዳሪያ ሠነድ ሳይከፈት ይመለስላቸዋል።
  14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም
  15. ከጨረታው ውድድር ውጪ ስለማድረግ፣ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚያሣይ ማሰረጃ እና የቫት /VAT/ ተመዘጋቢ ከሆነ የማስረጃው ፎቶ ኮፒ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ኮፒ ከማወዳደሪያው ሠነዳቸው ጋር ያላቀረቡ ተጫራቾች እንዲሁም ከዚህ በተጫራቹም መመሪያ ውጭ የሆነ አፈፃፀም ያላቸውና ከሚፈለገው መስፈርት በታች የሆነ ተጫራቾች ወዲያው ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  16. የሰው ኃይል አሰላለፍ ሂሣብ ምርመራ ኦዲት ሥራው ላይ የሚያሳትፋቸውን ባለሙያዎች ብዛት የት/ት ደረጃ የሙያ አይነትና በሙያው ያላቸውም ከዚህ በተያያዘው ቅፅ 03 ላይ በማያሻማ ሁኔታ መሞላት አለበት።
  17. የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት የጨረታው ውድድር እንደሚከተለው በሁለት ደረጃ የሚገመገም ይሆናል። ተጫራቹ ይህን በተመለከተ አግባብ ያለው መረጃ በቅጽ 01 እና በቅጽ 04 መሞላት ይኖርባቸዋል ።
  18. የዋጋ ማወዳዳሪያ 30% የሚያዝ ይሆናል። ይህም በተመለከተ አግባብ ያለው መረጃ በቅፅ 02 መሞላት ይኖርባቸዋል።
  19. ለቴክኒክ ብቃት እና ለዋጋ የተሰጡትን ነጥቦች በማዳመር በአጠቃላይ ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።
  20. የሥራ ፕሮግራም የአከፋፈል ሆኔታ፡-
    1. የአዲት ሥራውን ለማጠናቀቅና ሪፖርት ለማቅረብ የሚፈጅበትን ጊዜ ከሚያሰመራው የሰው ኃይል እና ከቴክኒካል ግምገማው ጋር ተገናዝቦ መቅረብ ይኖርበታል ።
    2. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቢመረጥ እና ውል ቢያዝ ሥራውን የሚጀምርበትንና የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ መግለጽ አለበት።
    3. የአከፋፈል ሁኔታ፣ በቅጽ 05 ተሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡
    4. ለማንኛውም ቅደመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ አለበት።
  21. የመወዳደሪያ ዋጋውን የምርመራ አገልግሎት ክፍያ እስከነታክሱ በትክክል ተሞልቶ መቅረዝ አለበት
  22. ሞጣ ከተማ ውኃ ፍሳሽ አገልግሎት / ድርጅት / የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የሞጣ ከተማ መጠጥና ውሃና አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender