የየም ልማት ማህበር የማህበሩን ሂሳብ ከሚያዚያ 01/2011 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2016 ዓ/ም ድረስ ያለውን የሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
የየም ልማት ማህበር
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የየም ልማት ማህበር የማህበሩን ሂሳብ ከሚያዚያ 01/2011 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2016 ዓ/ም ድረስ ያለውን የሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
2. በአዲት ሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው /ያላት፤
3. በሙያ ብቃትና በህጋዊነት ታውቀው በመንግስት የተመዘገቡ፤
4. የዘመኑን የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤
5. በአዲት ሥራ በቂ ሥራ ልምድና የሰው ኃይል ያላቸው፤
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አሥራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከ30/02/2018 ዓ/ም እስከ 21/03/2018 ዓ/ም ድረስ ለመመዝገቢያ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ሥራው የሚፈጀውን ጊዜና የዋጋ መግለጫውን በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስም በመጥቀስ እስከ 21/03/2018 ዓ/ም 10፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ኢት/ከልል የም ዞን ሳጃ ከተማ አስተዳደር በሚገኘው የልማት ማህበሩ ዋ/ጽ/ቤት በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
በተጨማሪ ጨረታው በቀን 22/03/2018 ዓ/ም 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በየም ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት በሳጃ ከተማ የጨረታ ኮሚቴ ፊት ለፊት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፦
- ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ - 0923430760/0942356962 ወይም 0934282235 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የየም ልማት ማህበር (የልማ)
