የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE (የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት)
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE
በድጋሜ የወጣ የደንብ ልብስ የጨረታ ማስታወቂያ
የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን መስቀል አደባባይ በሚገኘው የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ማግኘት ይችላል።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16 ኛው ቀን ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ብር 500 /አምስት መቶ/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) Exhibition Center & Market Development Enterprise በሚል አድራሻ ገንዘብ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በሎት በመለየት በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት በፊትና ከቫት በኋላ ያለው በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ይህ ጨረታ በድርጅታችን የግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለግዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማሳሰቢያ፡ ውድድሩ የሚካሄደው በሎት በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0115151693 መጠየቅ ይችላሉ።
የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት
