Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Transport and Road bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)
  • Address ዲላ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 131 60 04
  • Website
  • Deadline23 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-11-24 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከታች በቀረበው ሎቶች መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Transport and Road bureau (የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ቢሮ የተለያዩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከታች በቀረበው ሎቶች መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታው ላይ ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፦

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው /ያላት እና የ2018 በጀት አመት ግብር የከፈለ/ች/፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ/ች/፤ ህጋዊ ሰውነት፤ በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ኦንላይን አቅራቢ የሆነ
  • ሎት 1 የጽ/መሳሪያ ጨረታው ጨረታ ማስከበሪያ 21,000 /ሃያ አንድ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
  • ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ 80,000 /ሰማንያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በየሎቱ የተገለጸውን የጨረታ መስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ልክ 4፡00 ተሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል ይሁንና የሚቀጥለው 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ወይም የሣምንቱ መጨረሻ ቀን ቢሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾ የጨረታውን ዶክመንት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 204 በአካል ወይም በተወካይ በመቅረብ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ዶክመንት መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
  • እንዲሁም ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት አንድ ኦርጂናል ፋይናንሻል ዶክመንት እና አንድ ኦርጂናል ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 204 ለዚሁ ተግባር ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ሁሉም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል ይህ ሳይሆን ቢቀር የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ዶክመንት ሙሉ /የተሟላ ከሆነ ተጫራቹ ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታዎች ይከፈታሉ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል ይሁንና የቀረበው ናሙና የተበላሸ ወይም የማያገለግል ከሆኑ በራሱ ወጭ የመቀየር ግዴታ አለበት።
  • ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0903641061/0917961280 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ

 

Save Tender