የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
እነሱም
1ኛ ሎት እስቴሸነሪ /የጽህፈት መሳሪያዎች/
2ኛ ሎት የጽዳት እቃዎች ይህ ጨረታ በዘርፉ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው: የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ለምትችሉ ተጫራች ሁሉ ክፍት ነው።
- ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 5,000 ብር፣ ለጽዳት እቃዎች ሎት 2,500 ብር በኢትዮጵያ ከታወቀው ባንክ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300 /ሶስት መቶ/ የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ይ/ጨ/ከ/ግ/ን/አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚቀርበውና የሚፈጸመው በወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጪ / መዝጋቢ አካል የተሰጠ ህጋዊ ውከልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራች ለሚያቀርቡት እቃ የነጠላና የጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋናና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራች ንግድ ድርጅት ማህተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ይ/ጨ /ከ/ፋ/ግ/ን/አስተዳደር ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድር በመንግስት በስራ ቀን ብቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰዉ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በተራ ቁጥር 4 በተገለጸዉ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈተው 16ተኛዉ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በአል ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራች ባይገኝም በለሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከተጠቀሰዉ ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣዉ የመወዳደርያ ሀሳብ ወይም ሰነድ ተቀባይነት የለዉም ።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ለይርጋጨፌ ከተማ ፋይናንስ እቃዎችን ውል በገባበት ግዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የማጓጓዣ ወጭ በከተማ ፋይናንስ የሚሸፈን ይሆናል፤
- የከተማው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912063953 መደወል ይቻላል።
የይርጋ ጨፌ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
