በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዢ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡
በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዢ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡
በዚሁ መሠረት
ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች (ሲፒኦ) 10,000
ሎት 2 ሞተር ሳይክል (ሲፒኦ) 10,000
ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች (ሲፒኦ) 5000
ሎት 4 ደምብ ልብስ (ሲፒኦ) 5000
ከዚህ በላይ በሎት ተከፋፍሎ የተዘረዘሩት ዕቃዎች በዘርፉ የተሰማራችሁ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
- በዘርፉ ቀጥታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወቀረት፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ፎቶ ኮፕ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የ2017ዓ.ም ግብር የከፈሉበት የታክስ ክልራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ /VAT/ 15% ያካተተ መሆን አለበት፤
- ከ10,000 (አስር ሺህ) ብር በላይ ለሆነ ግዢ ዊዝሆልድንግ 3% ተግባራዊ ይደረጋል፤
- ተጫራቾች የ VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ከጠቅላላ ቫት ሂሳብ 7.5% ይቆረጣል።
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና (ሳምፕል) መ/ቤቱ በሚጠይቀበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን አይነት ዕቃ ላይ እንደሆነ በሠነዶቻችሁ እና በምታቀርቡት ፖስታ ላይ በትክክል ለይቶ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጣ የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) በአካውንት ቁጥር 1000521691305 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ አድቫይስ ይዞ መምጣት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 እና ለሎት 2 ብር 10,000(አስር ሺህ) ለሎት 3 እና ለሎት 4 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተሰራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለበት።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/አ/ስ/ስ/አመ/ር/ኮሚሽን ቢሮ ታርጫ ከቴሌ ቢሮ በስተጀርባ ከግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሮክቶሬት ቢሮ የጨረታ ዶክመንት መውሰድ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከሎት 1 እሰከ 4 ለተዘረዘሩ ጨረታ ለእያንዳንዱ ሎት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 1 በድምሩ 3 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/አ/ስ/ስ/አመ/ር/ኮሚሽን ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ16ኛው ሥራ ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክ/መ/አ/ስ/ስ/አመ/ር ኮሚሽን ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራች የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ጨረታ ዋጋ 10% (በCPO) በቅድሚያ በኮሚሽኑ ስም ማስያዝ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የበለጠ መረጃ፡ በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 09 20 92 50 53
አድራሻችን፡- ደ/ም/ኢ/ህ/ ክልል መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ታርጫ ከተማ ይገኛል።
በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
