የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ (የቢሮ ጥገና፣ የመጸዳጃ ቤት ጥገና የሴፕቲክ ታንክ ግንባታ) House Maintenance, Septic Tank Land scape, greenery & painting Work ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከንቲባ ጽ/ቤት በመናኸሪያ ክ/ከተማ ሚኒሊየም ቀበሌ የሚያሠራቸው (የቢሮ ጥገና፣የመጸዳጃ ቤት ጥገና የሴፕቲክ ታንክ ግንባታ/ House Maintenance, Septic Tank Land scape, greenery & painting Work/ ሥራ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት:
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ: GC -5 & BC -5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው -
በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣ በጨረታው እንዲሳተፍ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት
የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው -
የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ለሃያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር – 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20(ሃያ)ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም። ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከአምስት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሠንት (20% እስከ 30%) በታች ከሆነ በተሰበረው ተብለው ተይዞ የሚያልፍ ይሆናል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ
