በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ/ም በጀት ለሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የሚውል የመድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች (መሳሪያዎች)፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 ዓ/ም በጀት ለሆስፒታሉ አገልግሎት ላይ የሚውል የመድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች (መሳሪያዎች)፣ የላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ህትመቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የመድኃኒት ግዥ፣ ሎት ምድብ 01/2018
- ሎት 2 የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ፣ ሎት ምድብ 02/2018
- ሎት 3 የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሪኤጀንቶች ግዥ፣ ሎት ምድብ 03/2018
- ሎት 4 የአላቂ ቢሮ እቃ እስቴሽነሪ ግዥ፣ ሎት ምድብ 04/2018
- ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት ምድብ 05/2018
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣ ሎት ምድብ 06/2018
- ሎት 7 የህትመት ግዥ፣ ሎት ምድብ 07/2018
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስና ንብረት እስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻልና ቴክኒካል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 6፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462129560
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
