በኮ/ቀ/ክ/ከ/የወ/6/ጤ/ጣቢያ በጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም የተለያዩ መድሃኒቶች እና የህክምና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ
ለእያንዳንዱ ሎት መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ብር
ሎት 1-መድሃኒት እና የህክምና መሳረያ (20,000.00) ብር
በኮ/ቀ/ክ/ከ/የወ/6/ጤ/ጣቢያ በጨረታ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም የተለያዩ መድሃኒቶች እና የህክምና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም፡፡
1ኛ. በመንግስት እቃ አቅራቢነት ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የምስክር ወረቀት ያለው።
2ኛ. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ስም ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ግብር ከፋይ ቲን የምዝገባ ወረቀት ያላቸው ሆነው በዋጋ ዝርዝር ላይ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው፡፡
4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከቢሮ ቁጥር 47 መግዛት ይችላሉ፡፡
5ኛ. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና ለማቅረብ የማይመቹ እቃዎችን በፎቶ እና በካታሎግ ማቅረብ ወይም መስሪያቤቱ ድርጅቱ ድረስ ለሚልካቸው ኮሚቴዎች ተፈላጊ እቃዎችን ማሳየት ይኖርባችዋል፡፡
6ኛ. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መሙላት አይቻልም፡፡
7ኛ. ገዢው የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ድረስ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
8ኛ. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እና ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9ኛ. አሸናፊው ከታወቀ በሃላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
10ኛ. አሸናፊዎች በሰነዱ ውስጥ በተገለጸው ጊዜ ገደብ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ያሸነፉበትን 10% ሲፒኦ በማሰራት ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
11ኛ. ጨረታው የሚከፈተው በ 11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ በተቋሙ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
12ኛ. ተጫራቾች የሚያቀርቡአቸው እቃዎች የአገልግሎት ጊዜአቸው የሚያበቃበት ቀን ቢያንስ ከ አንድ ዓመት በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
13ኛ. የእያንዳንዱ ሎት ኦርጂናል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ መታሸግ ይኖርበታል፡፡
14ኛ. መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15ኛ. እስቶር እስከማስገባት ድረስ ያለውን የማጓጓዣና የጉልበት ወጪ ተጫራቹ ይሸፍናል
16ኛ. የጨረታ ማስከበሪያው በትክክል የተቋማችንን አድራሻ መግለጽ ይኖርበታል፡፡
17ኛ. ከአነስተኛ እና ጥቃቅን ጽ/ቤት የሚጻፉ ደብዳቤዎች በትክከል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ መሆኑ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ደብዳቤዎቹ በጽ/ቤቱ ሃላፊ ፊርማ እና ቲተር መውጣት ይኖርበታል።
18ኛ. በሚጫረቱበት እቃ ላይ እሴት ለሚጨምሩ ለአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ልዩ ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡
19ኛ. የጨረታው የስራ ቋንቋ የፌደራሉ የስራ ቋንቋ (አማርኛ) መሆን አለበት፡፡
20ኛ. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ኮልፌ ቀራኒዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቤተል ከአደባባዩ ዝቅ ብሎ ክፍለ ከተማው አጠገብ ወይም ፖስታ ቤት ፊት ለፊት፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 0118336993
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ
