Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሞጅ/ወ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለሞ/ጅ/ወ/ፍ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በአብክመ በሰ/ሸ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት የሞ/ጅ/ወ/ፍ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሞጅ/ወ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለሞ/ጅ/ወ/ፍ/ቤት እና ለጅሁር ንዑስ ወ/ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ፡-

  1. የሰራተኞች የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ብትን ጨርቅ
  2. የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪዎች
  3. ህትመቶች
  4. የተለያዩ የፅዳት እቃዎች
  5. የኤሌክትሮኒክስ የጥገና እቃዎች እና ሰርቪስ
  6. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች ግዥ
  7. የተለያዩ የቢሮ ቋሚ እቃዎችን ግዥ
  8. የተለያዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ጽሁፎች አቅርቦቶችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እያስታወቅን።

ሀ. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

ለ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር T/ ያላቸው

ሐ. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ ቫት ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከፊደል ሀ-ሐ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. የሚገዙ እቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  3. እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ 2% ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና Unconditional Bank Grantee/ ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ በፖስታ ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 03 ድረስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን እስከ 3፡45 ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል። ይህ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከናወናል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን በጥቅል ድምር /በሎት ስለሚያጫርት ሁሉንም እቃ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
  9. መ/ቤቱ በሚያጫርተው እቃ ላይ 20% ከፍ ወይም ዝቅ ብሎ የመግዛት መበት አለው።
  10. መ/ቤቱ ናሙና የሚፈልግ ከሆነ የማስቀረብ መብት አለው በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካልም ሆነ በስልክ ቁጥር 011 688 0091/42 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

በአብክመ በሰ/ሸ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት የሞ/ጅ/ወ/ፍ/ቤት

Save Tender