የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎች ግዢ ለመፈጸም ጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበት
- ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር/
- ለጽዳት እቃዎች ግዢ ብር 23,000.00 /ሃያ ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ 27/2/2018 ዓ/ም እስከ...11/3/2018 ዓ.ም. ከ11፡00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 12/3/2018. ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሣጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ፖ.ሣ.ቁጥር 1453
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን
