Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline05 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-12-05 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል የወንድ ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T582

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውል የወንድ ጫማ አምራች ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች በሙያ ዘርፉ ሶስት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰሩ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚመለከተው ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T582 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ90ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጫራቾችን የጨረታ ማስከበሪያ ለተጨማሪ ቀን የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘምለት የመጠየቅ መብት አለው።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ቅጂውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

 

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028/8025

ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com

 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender