በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የፅሁፍ ህትመት ስራ እንዲሁም የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የቋሚና አላቂ ዕቃዎች ግዥ ብሄራዊ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
ቋሚ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር፣ የፅሁፍ ህትመት ስራ እንዲሁም የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-
- ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፤
- የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስት/ 16 ቀን ከቀኑ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 12/03/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግዢ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1%(አንድ ፐርሰንት) በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም
በስልክ ቁጥር 033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
