የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል 1 (አንድ) እና ተርሚናል 2 (ሁለት) የመኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ለኤቲኤም ((ATM) እና ከታች ለተዘረዘሩት የተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎቶች በኪራይና በገቢ መጋራት አሰራር (concession Basis) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T581
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል 1 (አንድ) እና ተርሚናል 2 (ሁለት) የመኪና ማቆሚያ ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን ለኤቲኤም ((ATM) እና ከታች ለተዘረዘሩት የተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎቶች በኪራይና በገቢ መጋራት አሰራር (concession Basis) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
- ለኤቲኤም (ATM) አገልግሎት የሚውሉ ስድስት (6) ቦታዎች ላይ በሁለቱም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተርሚናሎች
- ለሚኒ ማርኬት (Mini market) አገልግሎት የሚውሉ ሁለት (2) ቦታዎች ላይ በሁለቱም የሀገር ውስጥ እና ዓለም እቀፍ ተርሚናሎች
- ለስጦታ እና የአበባ መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ - ሁለት (2) ቦታዎች ላይ በሁለቱም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተርሚናሎች
- ለቴሌ ሴንተር እና የፎቶ ኮፒ አገልግሎት የሚውሉ – ሁለት (2) ቦታዎች ላይ በሁለቱም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተርሚናሎች
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ከላይ በተጠቀሱት የአገልግሎት ዘርፎች ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በመንግስት ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T581 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ፣ የጨረታ ቁጥር፣ የሚጫረቱበትን የአገልግሎት ዘርፍ ወይም ዘርፎች፣ የድርጅቱን ስም እና ስልክ ቁጥር ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
በጨረታው የሚካፈሉ ማንኛውም ተጫራቾች ለ120 ቀናት የሚቆይ አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond)፣ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፋት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ቅጂውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን በ9፡30 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በስልክ ቁጥር: +251-115-17 89 18 ኢ-ሜይል፡ EskedarG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
