Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)
  • Address Ras Mekonen Street, Leghar behind Ethiopian Insurance Corporation H.Q., Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 251115549300
  • Websitehttps://www.eslse.et/
  • Deadline11 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-11 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Transportation Service And Cargo

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በድርጅታችን በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ እየተከናወነ ካለው የወደብ መሰረተ-ልማት ሥራ ጋር ተያይዞ ፈርሰው የተቀመጡ ኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) እና በድርጅታችን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ጉዳት የደረሰባቸውን 5 ባለ አርባ ጫማ እና 13 ባለ 20 ጫማ በድምሩ 18 የተጎዱ ኮንቴይነሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)


 

ያገለገሉ የኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) እና ያገለገሉ እና የተጎዱ ኮንቴይነሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር - DIS 01/2018

 

በድርጅታችን በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ እየተከናወነ ካለው የወደብ መሰረተ-ልማት ሥራ ጋር ተያይዞ ፈርሰው የተቀመጡ ኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) እና በድርጅታችን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ጉዳት የደረሰባቸውን 5 ባለ አርባ ጫማ እና 13 ባለ 20 ጫማ በድምሩ 18 የተጎዱ ኮንቴይነሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ድርጅት/ ግለሰብ በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለመጀመሪያ ቀን ከወጣበት ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 8 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ከማክሰኞ ጥቅምት 25 እስከ ሰኞ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ጨረታው እስከሚታሽግበት ማክሰኞ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30 ሰዓት እስከ ከ8፡00 ሰዓት በፊት የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና የገዙበትን ማስረጃ በመያዝ ፈርሰው የተቀመጡ ኬ ስፓን ሼድ (K SPAN SHADE) በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል እንዲሁም የተጎዱ ኮንቴይነሮችን በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ከላይ ለሰነድ ሽያጭ በተቀመጠው ቀን እና ሰዓት መሰረት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ማክሰኞ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ሰነድ የዝዙ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ እስከ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-5-54-92-57/ 09-51-41-42-04 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

 

Save Tender