የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.ስ.ጉ.ማ.ፌ) የ2025 ሒሳቡን በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
Federation of Ethiopian Associations of Persons with Disabilities (የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን) (ኢ.አ.ጉ.ማ.ፌ)
የሒሳብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢ.ስ.ጉ.ማ.ፌ) እ.ኤ.አ. በታህሳስ 1996 የተመሠረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ መንግስታዊ ያልሆነ በተለያየ የአካል ጉዳት የተደራጁ ማህበራት ጥምረት ነው። ፌዴሬሽኑ እ.ኤ.አ. ነሐሴ ወር 2019 በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1113/2019 መሰረት በምዝገባ ቁጥር 1511 ዳግም ምዝገባ በማድረግ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በአሁኑ ወቅት ፌዴሬሽኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ 38 የሚሆኑ አባል ማህበራት ሕብረት ነው።
ፌዴሬሽኑ እ.ኤ.አ. የ2025 ሒሳቡን በውጭ ኦዲተሮች ማስመርመር ስለሚፈልግ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።
- ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራት የተመዘገቡ፣
- መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሒሳብ ምርመራ ልምድ ቢኖራቸው ይመረጣል፤
በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ25 - 30 የሚሆኑ የሰነድ ፋይሎች (Box File) ለመመርመር የሚሠሩበትን ዋጋ እና ሥራው የሚፈጅባቸውን ጊዜ በመጥቀስ የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ወደናይጄሪያ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ መግቢያ በር ፊት ለፊት በሚገነጠለው አስፋልት ከ60 - 70 ሜትር ያህል ገባ ብሎ በሚገኘው መ/ቤታችን የሰው ኃብት አስተዳደር ረዳት ክፍል ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011 - 155 30 03 ወይም 0965 - 48 07 65 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
