የደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች እና የተሽከርካሪ (የመኪና) ማስዋቢያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
South Nation Nationality of Peoples Regional State Construction Autority (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የኮንስትራክሽን ባለስልጣን)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች እና የተሽከርካሪ (የመኪና) ማስዋቢያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- በገቢዎች ባለስልጣን የምዝገባ ሠርተፍኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በአካል በመቅረብ ለያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት ለጽዳት እቃዎች፣ ለጽህፈት መሳሪያ፣ ለተሽከርካሪ ማስዋቢያ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ለኤሌክትሮኒክስ ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤቨሎፕ በአስራ አምስተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፣
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በ8:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ለጽህፈት መሳሪያ 10,000.00 (አስር ሺብር)፣ ለጽዳት ዕቃዎች 3,000.00 (ሶስት ሺ ብር)፣ ለተሽከርካሪ ማስዋቢያ 3,000.00 (ሶስት ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በካሽ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታ ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ብቻ መጠቀም አለባችሁ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንስትራክሽን ባለስልጣን
