በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ከዚህን በፊት በወረዳው ውስጥ የገጠር መንገድ ተደራሽነት (URRAP) ፕሮግራም ተሰርተው የነበሩትን የገጠር መንገዶች በ2018 ዓ/ም በሕዝብ ተሳትፎ በጀት እና በወረዳው በጀት የጥገና ሥራ መስራት ይፈልጋል።
በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት ከዚህን በፊት በወረዳው ውስጥ የገጠር መንገድ ተደራሽነት (URRAP) ፕሮግራም ተሰርተው የነበሩትን የገጠር መንገዶች በ2018 ዓ/ም በሕዝብ ተሳትፎ በጀት እና በወረዳው በጀት የጥገና ሥራ መስራት ይፈልጋል። ለዚሁ ሥራ የሚሆን ዶዘር (D8R)፣ ግሬደር (CAT)፣ ኤክስካቫተር (CAT)፣ ሮለር (DYNAPAC 14TON)፣ ሻወር ትራክ እና የሲኖትራክ ገልባጭ መኪና (16 M3) ባለንብረቶችን የወረዳው ገ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- ህጋዊ የአከራይ ፍቃድ ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ያሳደሰ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 ብር /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረዳው ገ/ጽ/ቤት በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ይህ ጨረታ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም ዓ.ም ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል።
ማሳሰብያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- የመ/ቤቱ የእጅ ስልክ 09 22 71 12 25
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ መንገዶች እና ሎጀስቲክስ ጽ/ቤት
