Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Regional State Culture, Tourism & Sport Bureau (የሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-4924
  • Websitehttps://visitsidama.travel/
  • Deadline25 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security10,000 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-11-25 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Stationery Materials , Electronics Materials

የሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስና ስቴሽነሪ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Sidama Regional State Culture, Tourism & Sport Bureau (የሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

የሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስና ስቴሽነሪ ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

መለኪያው

ምርመራ

1

ሎት አንድ፡- ኤሌክትሮኒክስ

በቁጥር

የሎት 1፣ 2 እና ሎት 3 ዕቃዎች ብዛትና እና አይነት ዝርዝር መረጃ በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል

2

ሎት ሁለት፡- ፈርኒቸር

በቁጥር

3

ሎት ሦስት፡- ስቴሽነሪ

በቁጥር

 

  • ተጫራቾች የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ማስረጃዎቻቸውን በግልፅ ሊነበቡ በሚችል መልኩ አደራጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ሎግታ አጠገብ ሲዳማ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 18 ሀዋሳ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት CPO ለእያንዳንዳቸው ለሎት አንድ፣ ለሎት ሁለት እና ለሎት 3 ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ /ፕሮፎርማ/ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒና ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀ ላጥን ውስጥ ጨረታው ከታወጀበት እስከ 15ኛው የሥራ ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቶች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 ሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሎግታ አጠገብ ሀዋሳ ይከፈታል፡፡
  • መ/ቤቱ ከጠቅላላው የግዥ መጠን /ብዛት/ ላይ 20% ሊጨምር ወይመ ሊቀነስ ይችላል፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ነገር ግን የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት እና የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ባይሆን የጨረታው ሳጥን የማሸጉም ሆነ የመክፈት ሥነ-ሥርዓት የሚከናውነው በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር፡- 046-212-4924 ወይም 0462124615 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

የሲዳማ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

 

Save Tender