የጋምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጋምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
1. የሕክምና እቃዎች እና መድኃኒቶችን፣
2. ተኝቶ ለሚታካሙ ሕሙማኖች ምግብ ቁርስ፣ ምሳና እራት የሚያቀርብ፣
1. በጨረታው ለመሳተፍ የምፈልጉ ተጫራቾች ለጨተታ ጋምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአስፓልት ወደ ውስጥ 18 ኪ.ሜ ገባ ስለሚል ሰነዱን በመልካ ኦዳ አጠቃላይ ሆስፒታል በኩል በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት በነጠላ ወይም በጥቅል ለመጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታው ሰነዱ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በማሸግ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሲሆን ሲፒኦ በባንከ የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡
4. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታላችን ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅርብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ. ከሚቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ገቢዎች የምዝገባ የምስክር ወርቀት፤
ለ. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ15 ቀን ይሸጣል፡፡
ሐ. ከፌዴራል ሃገር ውስጥ ገቢ ወይም ከከልሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብርግዴታዎችን የተወጡና በጨረታው መካፈል የምችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ አቅርቦት የምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
መ. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ቲን /TIN/ ማቅርብ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በከፊልም ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
ሠ. ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ መጠን በጨረታ መመሪያ ላይ የተገለጸ ሲሆን ሲፒአውን ከኦሪጅናል ሰነድ ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታው ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ረ. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ያልተመታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ሰ. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሸ. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ከቢሮ ጋር ውል በመፈራርም በተፈራረመው ውል መሠረት ዕቃውን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ስልክ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 09-12-30-45-08/09-13-52-49-51
ጋምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል
