Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት
  • Address ሃይሌ ጋርመንት አደባባይ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline02 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-12-02 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works , Contractors

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የፈዴራል መንግሥት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 መሰረት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸዉ የት/ቤቶች ግንባታ ጤና ጣቢያ ግንባታ፣ ሼዶች ግንባታ፣ ህፃናት ማቆያዎች እና ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ስራዎችን በሀገር ውስጥ ተቋራጮች እና ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: NSLSCDCO/002/2018

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የፈዴራል መንግሥት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 መሰረት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸዉ የት/ቤቶች ግንባታ ጤና ጣቢያ ግንባታ፣ ሼዶች ግንባታ፣ ህፃናት ማቆያዎች እና ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ስራዎችን በሀገር ውስጥ ተቋራጮች እና ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ፕሮጀክቶችን ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

  1. ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ (supplier list) ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው የሚያስገቡት የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶች እያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታ ላይ ፊርማ፣ ፕሮጀክት ስምና የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና ፋይናንሽያል አንድ ኦሪጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የታሸጉትን ሶስት ቴክኒካል ሰነዶች በአንድ ላይ በማሸግ እና ሶስቱን ፋይናንሻል ሰነዶች በአንድ ላይ በማሸግ ሁለቱን የታሸጉ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond or Bid Security) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ስም፣ ፊርማ፣ ማህተም በማድረግ ከኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ከታች በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሃያ አንድ (21) ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን 5ኛ ወለል በቢሮ ቁጥር 3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ ለማህበራት ነጻ እንዲሁም ለተቋራጮች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተቋራጭ እስከ 22ኛው ቀን እና ለማኅበራት እስከ 23ኛው የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 22ኛው እና 23ኛው የስራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ከሎት ከ11-18 ለ60 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond or bid security) እና ከሎት ከ19-24 ለ120 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond or bid security) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee/ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ለማኅበራት ከተደራጁበት ወረዳ ኦርጅናል ዋስትና ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ዋጋ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
  6. ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
  7. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተ.ቁ

የፕሮጀክቱ ስም

ፕሮጀክቱ የሚገኝበት ቦታ ወረዳ

ልዩ ቦታ

ብዛት

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን/ ደብዳቤ

ማህበራት እና ተቋራጭ ደረጃ

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ሎት

1

ደረቅ ምግብ ዝግጅት

07

ቡና ቦርድ አካባቢ

1

 

 

 

ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና ደብዳቤ

ጀማሪ ምህበራት

21 ቀናት

1

2

ደረቅ ምግብ ዝግጅት

07

ቡና ቦርድ አካባቢ

1

ጀማሪ ማህበራት

21 ቀናት

2

3

ደረቅ ምግብ ዝግጅት

05

ጎፋ ኮሌጅ አካባቢ

1

ጀማሪ ማህበራት

21 ቀናት

3

4

እንጨት እና ብረታ ብረት

05

ኢንዱስትሪ መንደር

1

መብቃት

21 ቀናት

4

5

እንጨት እና ብረታ ብረት

07

ቤተሰብ መምሪያ

1

መብቃት

21 ቀናት

5

6

እንጨት እና ብረታ ብረት

02

ቆሬ

1

መብቃት

21 ቀናት

6

7

ከተማ ግብርና

02

ቆሬ ኢንዱስትሪ መንደር

1

መብቃት

21 ቀናት

7

8

ዶሮ እርባታ ሼድ

05

ሰንጋ ተራ

1

ታዳጊ ማህበራት

21 ቀናት

8

9

ዶሮ እርባታ ሼድ

05

ሰንጋ ተራ

1

ታዳጊ ማህበራት

21 ቀናት

9

10

ዶሮ እርባታ ሼድ

05

ሰንጋ ተራ

1

ታዳጊ ማህበራት

21 ቀናት

10

11

ህፃናት ማቆያ

13

ስፖንጅ ፋብሪካ ጀርባ-ቀጠና 06

1

200,000

BC-6/GC-7/ ተመራቂ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

11

12

ህፃናት ማቆያ

08

ክርስቶስ አምባሳደር ቸርች ፊት ለፊት

1

200,000

BC-6/GC-7/ ተመራቂ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

12

13

ህፃናት ማቆያ

11

ገብርኤል ሰፈር ጸደይ ልማት ተነሽ አካባቢ

1

200,000

BC-6/GC-7/ ተመራቂ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

13

14

ህፃናት ማቆያ

14

ማህበር ቤቶች ጎን

1

200,000

BC-6/GC-7/ ተመራቂ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

14

15

ወረዳ 06 ስፖርት ሜዳ

06

ወረዳ 06 ቄራ ከብት በረት ፊትለፊት

1

300,000

BC-5/GC-6/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

15

16

ወረዳ 10 አሸዋ ሜዳ ስፖርት ሜዳ

10

ወረዳ 10 ቀይ አፈር ብሄረጽጌ

1

300,000

BC-5/GC-6/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

16

17

ወረዳ 09 ስፖርት ሜዳ

09

ወረዳ 09 አስተዳደር ህንጻ ጀርባ

1

300,000

BC-5/GC-6/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

17

18

ወረዳ 12 ስፖርት ሜዳ አጥር ግንባታ

12

ወረዳ 12 ወጣት ማዕከል ግቢ ውስጥ

1

300,000

BC-5/GC-6/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

18

19

ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ጂ+5 ህንጻ

09

ካዲስኮ አካበቢ

1

300,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

19

20

ሃና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 ህንጻ

14

ወረዳ 14 ሰፈራ

1

500,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

20

21

ለቡ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 ህንጻ

14

ሀጫሉ መንገድ ኖክ ማደያ ጀርባ

1

500,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

21

22

ቆጣሪ ቁጥር 1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 መማሪያ ህንጻ

11

ወረዳ 11 አስተዳደር አካባቢ

1

500,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

22

23

አጼ ዘረያእቆብ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ጂ+4 መማሪያ ህንጻ

06

ቄራ ሶፊያ ሞል ፊት ለፊት ገባ ብሎ

1

500,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

23

24

አጼ ዘረያእቆብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጂ+4 መማሪያ ህንጻ

06

ቄራ ሶፊያ ሞል ፊት ለፊት ገባ ብሎ

1

500,000

BC-4/GC-5/ እና ከዚያ በላይ

21 ቀናት

24

 

ማሳሰቢያ፡-

  • አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በመረጠው አንድ ሎት ብቻ ይሆናል። ከአንድ ሎት በላይ ተወዳድሮ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
  • ጨረታ ሰነዱ ለማስገባት የሚቀርቡ ተጫራቾች ህጋዊ መታወቂያ ወይም ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና እና መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ፋይናንሻል ሰነዱ ሲሞሉ ለሚገጥም ስርዝ ድልዝ ጨረታው ከመዘጋቱ ከ5 ቀን በፊት ለአንድ ጊዜ ብቻ የገዙትን ፋይናንሻል ሰነድ መቀየር የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት 5ኛ ህንፃ ላይ ቢሮ ቁጥር 3 በጽሑፍ ጥያቄ መቅረብ ይችላሉ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

አድራሻ ፡- ሃይሌ ጋርመንት አደባባይ

 

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት

 

Save Tender