በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ በጀት ለከለላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት-1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት፣ ሎት 3. የግንባታ ማቴሪያል እና ሎት-4. ኤሌክትሮኒክስ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በመደበኛ በጀት ለከለላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት-1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ዓመታዊ የመኪና ስፔር ፓርት፣ ሎት 3. የግንባታ ማቴሪያል እና ሎት-4. ኤሌክትሮኒክስ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
3. የግዥ መጠን ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ለየብቻ ለአመታዊ ስፔር ፓርት ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለሌሎቹ ለእያንዳንዳቸው ሎቶች 30,000/ ሰላሳ ሺህ/ ብር በጥሩ ገንዘብ በመሂ 1 (ደረሰኝ) ወይም በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊነታቸው ከታወቀ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ በከለላ ወረዳ ዓቃቢ ሕግ ጽ/ቤት ውል በመግባት በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ኦርጅናል እቃ ማቅረብ አለባቸው።
7. አሸናፊው ድርጅት በውላቸው መሰረት የመኪና አመታዊ ስፔር ፓርት እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም እንደ አስፈላጊነታቸው የሚቀርብ ሲሆን ሌሎቹን ሎቶች ግን ከለላ ወረዳ ሴክተር መቤቶች ድረስ ማስጫኛና ማውረጃ ጨምሮ በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነዱን ከከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ 200/ ሁለት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፣ የጽህፈት መሳሪያ ሳምፕልን አስመልከቶ ግዥ ቢሮ ቁጥር 04 መመልከት ይችላሉ፡፡
9. የውድድሩ ሁኔታ በጠቅላላ ድምር በሎት ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከላላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡-0914612251/0334510464 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
11. ማንኛውም ተጫራች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ጠቅላላ ድምር በማስቀመጥ የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
12. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር04 በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው _በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዢ ይሆናሉ፡።
13. የጨሪታ መከፈቻ ጊዜ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
14. መ/ቤቱ የእቃውን 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
15.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የከለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
