የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉና ለማህበረሰብ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም የምግብ ግብአቶች፣ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ የህክምና ኦክሲጅን ጋዝ እና አንሶላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ድሬዳዋ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-/ድ/ዳ/ሣ/ጠ/ሆ 02/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉና ለማህበረሰብ ፋርማሲ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም የምግብ ግብአቶች፣ የመድሃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ የህክምና ኦክሲጅን ጋዝ እና አንሶላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በመንግስት ግዢ አቅራቢነት የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ /ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለሰ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቁጥር 03 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ ተመሰከረለት ቼክ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎ በማድረገ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጃ የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸለት አስፈላጊውን ውል ማከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተማላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ሆስፒታሉ የተለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0251124968 /0912058798 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል
