Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ውሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 116 01 99
  • Website
  • Deadline17 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየሚጫረቱበትን ለቁርጥራጭ ብረታ ብረቱ እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሳሪያዎች የሚሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በተናጠል 10%
  • opening date2025-11-18 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles , Used Items

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሳሪያዎች በንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 2/2/2003 መሰረት መ/ቤታችን በሽያጭ አወዳድሮ ማስወገድ ይፈልጋል።

በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሳሪያዎች በንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 2/2/2003 መሰረት መ/ቤታችን በሽያጭ አወዳድሮ ማስወገድ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት አሟልታችሁ መጫረት ትችላላችሁ፡፡

  1. ተጫራቾች ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሰሪያዎችን በወረኢሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በመገኘት የፈቃድ ደብዳቤ በመያዝ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሰሪያዎችን በሚገኙበት መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  2. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤታችን በመገኘት ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ ማለትም ለቁርጥራጭ ብረታ ብረቱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ለቁርጥራጭ ብረታ ብረቱ እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጡ የግብርና መሳሪያዎች የሚሞሉበትን ጠቅላላ ዋጋ በተናጠል 10% የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእቃ ዓይነት መጠንና ብዛት እንዲሁም የእቃውን ሁኔታ በአካል በቦታው በመገኘት ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ፖስታ በአካል ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአካባቢ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በይፋ ይከፈታል፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው።
  7. ለበለጠ መረጃ የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር፡- 0331160199/54 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይንም በሕዝብ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

 

 

Save Tender