Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ ግዥ፣ ሎት 5 የተለያዩ የጥገና እቃዎች ግዢ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ፣ ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ ግዥ፣ ሎት 5 የተለያዩ የጥገና እቃዎች ግዢ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማደመሰስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዲስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዢ ዴስክ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።
  6. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በስል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ ለሎት 01 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሁለት ሺ ብር)፣ ለሎት 02 የፅዳት እቃዎች ግዥ ብር 24,000.00 (ሃያ አራት ሺ ብር)፣ ሎት 03 የደንነት መጠበቂያ እና የደንብ አልባሳት ግዥ ብር 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺ ብር)፣ ለሎት 04 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ብር 90,000.00 (ዘጠና ሺ ብር)፣ ሎት 5 የተለያዩ የጥገና እቃዎች ግዢ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) ለ5ቱም ሎት ለየብቻ የተሰራ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ከጥቅምት 23 ቀን 2018 እስከ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም።

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ

 

Save Tender