Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የምያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ /ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይከል እና የተሸኸሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች፣ ኮስሞቲከስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ሲሚንቶ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 14/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የምያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ /ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይከል እና የተሸኸሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች፣ ኮስሞቲከስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ሲሚንቶ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳውቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘውትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ አስከ አርብ ከ2፡00 -12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (እንድ መቶ ብር) በመከፈል በጽ/ቤታችን የዕለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ ( 5 ) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንከ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወከሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፈት ይከፈታል፡፡

5.ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡

6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠርበ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፤

7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ይሆናል፡፡

 

8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋርየሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት C.O.P ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

11 ጽ / ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችልሉ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender