በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት /ወይን አምባ/
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ባለው ዝርዝር መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- ሎት 1 ፡- የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 3 ፡- የጽዳት እቃ
- ሎት 4 ፡- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 5 ፡- የመኪና ጎማዎች
- ሎት 6 ፡- የመኪና ዘይትና ቅባት
ስለዚህ
- በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) ያላቸው እና ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሎት 1 ሃያ አምስት ሺህ ብር (25,000)፣ ለሎት 2 አስር ሺህ ብር (10,000) ፣ ለሎት 3 ሁለት ሺህ ብር (2,000)፣ ለሎት 4 ሰማኒያ ሺህ ብር (80,000)፣ ለሎት 5 ሃያ ሺህ ብር (20,000) እና ለሎት 6 አስር ሺህ ብር (10,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ ስም በግልጽ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ጨረታው ይከፈታል፣ የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ባይገኙም የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው የሚወዳደረው በጥቅል ዋጋ ነው። በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከመውሰዱ በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ በለገሂዳ ወረዳ ስር ባሉት መ/ቤቶች በየንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ ዕቃዎቹን ርከከብ ሲፈጽም ጥራቱን በባለሙያ ተረጋግጦ የታሸጉ ዕቃዎችን ተፈተውና ታይተው ተቆጥረው ተለክተው ገቢ መሆን አለባቸው፣ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ከሆነ በ5 ቀናት ውስጥ መልሶ መተካት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ የውለታ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ሆኖ በውለታ ሰነድ ላይ ዝርዝሩ ይቀመጣል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ጥራት ያለው እና ኦርጅናል መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0914364932 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
- የወረዳችን ከተማ ከደ/ወሎ ዞን ምዕራብ አቅጣጫ በ103 ኪሜ ላይ ትገኛለች፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለናሙና ያስቀመጥናቸውን እቃዎች ከግዥ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ለተከታታይ 60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
ማሳሰቢያ፡- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪ ስርዝ ድልዝ እና አሻሚ የሆነ ቁጥር ካለ ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት /ወይን አምባ/
