Tender Detail

Tender Details


የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የአባሎች/ ሰራተኞች መዝ/ክበብ እና የህግ ታራሚዎች ህ/ሱቅና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ የአትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች፣ የፅዳትና የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የታሸገ የመጠጥ ውሃ እንዲሁም የፅህፈት መሳሪያትን እና የተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል።

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የአባሎች/ ሰራተኞች መዝ/ክበብ እና የህግ ታራሚዎች ህ/ሱቅና መዝናኛ ክበባት አገልግሎት የሚውሉ የአትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች፣ የፅዳትና የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የታሸገ የመጠጥ ውሃ እንዲሁም የፅህፈት መሳሪያትን እና የተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ግብዓቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፈው ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፣ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዥና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት የተጨማሪ እሴት ታክስ (ካት) ተመዝጋቢ የሆኑ እና መለያ ቁጥር (TIN Number) ተጋቢ የሆኑና የተሟላ ማስረጃ በ2 ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን አንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በእያንዳንዱ ሰነድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007972397 አ/አ/ ማረ/ቤት የህ/ታራ/ህ/ሱቅ በሚል ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የህ/ሱቅ/መዝ/ክ/ክ/ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ላይ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ማረ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
  3. ተጫራቾች ከላይ በጨረታ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲያቀርብ የተጠየቀባቸው ናሙናውን በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነድ መግዛትና የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት በማረ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤቱ በሚያዘው ትዕዛዝ መሰረት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል በሚገኘው ዕቃ ግ/ቤት አምጥተው ያስረክባሉ፡፡
  8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  9. ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ መይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፤ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ተቀባይነት የለውም። በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 

አድራሻ፡- ገላን

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 011-4-71-71-21 ይደውሉ።

 

የከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል

 

Save Tender