በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሻሸመኔ ሪጅን ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለማሰፋት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የስፌት አገልግሎቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሻሸመኔ ሪጅን መ/ቤት
የደንብ ልብስ ለማስፋት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU/SHR-002/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሻሸመኔ ሪጅን ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለማሰፋት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የስፌት አገልግሎቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
ብዛት |
ጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
1 |
ባለገበር ኮትና ሱሪ |
314 |
ብር 45,920.60
|
|
2 |
ባለገበር ኮትና ጉርድ ቀሚስ |
110 |
|
|
3 |
ጃኬት እና ሱሪ |
1552 |
|
|
4 |
ኮትና ጉርድ ቀሚስ |
226 |
|
|
5 |
ጋወን |
157 |
|
|
6 |
ቱታ |
67 |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው (በኤጀንሲው ድረ-ገፅ http://www.ppa.gov.et ላይ የተመዘገበ) የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት ቁጥር (TIN) ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሻሸመኔ ከተማ ሞቢል፣ ከብሄራዊ ሎቶሪ ፊት ለፊት በሚገኘው ማሞ ኑራ ህንፃ ላይ፣ ሻሸመኔ ሪጅን ጽ/ቤት ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት እና PGS ቢሮ ቁጥር 201 የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል ወይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) አካውንት ቁጥር 100025644933 በማስገባት እና ስሊፑን በማቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 45,920.60 (አርባ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ብር ከ60/100) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሻሸመኔ ከተማ በሚገኘው የሪጅኑ ጽ/ቤት ሰፕላይ ቼይን እና PGS ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር (046) 211 3001 መደወል ይችላሉ።
- ሪጅኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሻሸመኔ ሪጅን መ/ቤት
