Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0256660691
  • Websitehttps://ess.gov.et/am
  • Deadline08 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-11-08 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት


 

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ሀረ/ግ/ጨ/001/2018

 

መ/ቤታችን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

የግዥው ዓይነት መግለጫ

 

የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ)

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር

1

የቢሮ ኪራይ ጨረታ ለሁለት አመት የሚቆይ

100.00

5,000.00

 

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራን ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
  5. ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን (በዕለቱ) 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
  6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

ስልክ ቁጥር፡- 0256660691/0912806409

 

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender