በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የትም/ትና ስልጠና የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የህሙማን ቀለቦች፣ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች እና ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቆችን (አቡጀዲ) እና የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የትም/ትና ስልጠና የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የህሙማን ቀለቦች፣ የተለያዩ የፅዳት እቃዎች እና ለፅዳት አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቆችን (አቡጀዲ) እና የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ህጋዊ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በጨረታው ለመወዳደር በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ነምበር)፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ እንዲሁም ወርሃዊ የቫት ሪፖርት ገቢ ያደረጋችሁበትን ደረሰኝ (በጨረታ እንድትሳተፉ የተሰጣችሁ የገቢዎች ደብዳቤ) ማቅረብ የምትችሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መጫረት እንደምትችሉ እየገለፅን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በምዕራብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጊዜያዊ መኖሪያ ካምፕ በጊንጪ ከተማ በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ። ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ለተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር)፤ በአላቂ የፅህፈት መሳሪያ እና ለትም/ትና ስልጠና ብር 57.500.00 (ሃምሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)፤ ለህሙማን ቀለብ ብር 137,590.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ብር)፤ ለተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች ብር 106,900.00 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር) እና ለተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO በጥሬ ገንዘብ (በካሽ) በቼከ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት እንዲሁም የተቀመጠውን መመዘኛ ካሟሉ በሌሉበት በምዕራብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጊዜያዊ መኖሪያ ካምፕ በጊንጪ ከተማ ይከፈታል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 09-12-94-67-70/ 09-08-06-50-70 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በምዕ/ብ ዕዝ የ401ኛ ኮር ጠቅላይ መምሪያ
