Tender Detail

Tender Details

  • Company ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር
  • Address ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0965683654
  • Website
  • Deadline07 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-11-07 00:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

ሐበሻ ቢራ አከሲዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል።

ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር


ሐበሻ habesha

ነጭ የተጣራ ስኳር ግዢ የጨረታ ማሳወቂያ

ሐበሻ ቢራ አከሲዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅቶች ጋር ለምርት ግብአት የሚሆን ነጭ የተጣራ ስኳር ለማቅረብ ተፈራርሞ መስራት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች -

  • ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ፣ ለምግብ እና መጠጥ ምርት ተስማሚ የሆነ ነጭ የተጣራ ስኳር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ስኳሩ ከብከለት የጸዳ መሆኑን፣ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫዎችን የተከተለ እና እርጥበትን መቋቋም በሚችል ማሸጊያዎች መታሸጉን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።
  • 4 ሚሊዮን ኪሎ (4,000 ቶን) ስኳር ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል፡፡
  • በስራ ላይ ምንም አይነት መስተጓጎል አለመኖሩን ለማረጋገጥ በቅድመ-ስምምነት መሰረት ስኳሩን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  • ንጽህና፣ የእርጥበት መጠን እና ጎጂ ንጥረ ነገሮች አለመኖር ያሉ የጥራት መለኪያዎችን ለማረጋገጥ ለእያንዳንዱ ባች የትንታኔ ሰርተፍኬት (certificate of Analysis) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጉድለት ያለባቸውን አቅርቦቶችን ያለምንም ተጨማሪ ወጪ መተካት ይኖርባቸዋል።
  • በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት ሊኖራቸው ይገባል።
  • ተጫራቾች ወደዋና መስሪያ ቤት በመምጣት እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 7፡00 ሰዓት (ሰባት ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 500 ብር በመከፈል የጨረታ ሰነድ መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት (ስምንት ሰዓት) ድረስ ተጫራቾች በአካል ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ወይም በኢሜል አድራሻ factoryprocurement@ habeshabreweries.com በመጠቀም ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ድርጅቱ ምላሾቹ ከተቀበለ በኋላ የጨረታ ሰነዶችን በመገምገም የተመረጡትን/ያሸነፉትን አቅራቢዎችን ያሳወቃል።

አድራሻ፡ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር

ቦሌ ካርጎ ፊት ለፊት

ስ.ቁ. 0965683654/0911478704

አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር  

Save Tender