Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline31 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-31 00:00:00
  • Categories Building Materials , Construction Materials And Raw Materials

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የጠጠር መንገድ ሥራ ለመሥራት ሰሌክት ማቴሪያል ግዥ ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የጠጠር መንገድ ሥራ ለመሥራት ሰሌክት ማቴሪያል ግዥ ስለተፈለገ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ድርጅት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ኮንስት/ ማቴሪያል አቅራቢነት ዘርፍ፤
  2. በሥራ መስኩ ሀጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (አስር) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ወስዳችሁ ዋጋ ሞልታችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  7. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር፡- 046-2-20-99-63/046-2-12-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ

 

Save Tender