Tender Detail

Tender Details

  • Company ኦጋዴን እርዳታና ልማት ድርጅት
  • Address , Phone: +251915100231
  • Website
  • Deadline25 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-10-25 00:00:00
  • Categories Audit Service

ኦጋዴን እርዳታና ልማት ድርጅት እ.ኤ.አ በ2024 የበጀት ዓመት ያከናወናቸው ሥራዎች እና የሂሳብ ሰነድ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል

ኦጋዴን እርዳታና ልማት ድርጅት


ለኦዲት ስራ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ኦጋዴን እርዳታና ልማት ድርጅት የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሰርተፊኬት ቁጥር 6791 የተመዘገበ ሲሆን፤ የአርብቶአደሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን በድርቅና በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ የሚጎዱ ወገኖች ለመርዳትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በትጋት በመስራት በተለያዩ የሶማሌ ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ሁለት (2) አመታትም እንደዚሁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በሶማሌ ክልል በፋፈን እና ቆራሄ ዞኖች በጅግጅጋ እና ኩዱንቡር ወረዳዎች ሦስት መቶ (300) ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ዙሪያ እንዲሁም በንጽህ መጠጥ ውሃና ጽዳት (WaSH) ዙሪያ ወሳኝ ስልጠናዎች ሰጥቷል።

በዚህ መሠረት ድርጅታችን እ.ኤ.አ በ2024 የበጀት ዓመት ያከናወናቸው ሥራዎች እና የሂሳብ ሰነድ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ድርጅቱ እንዲመረመርለት ያቀረበው የቦክስ ፋይል ብዛት በቁጥር 03 (ሶስት) ሲሆን ለመወዳደር የሚፈልግ ኦዲተር/ ኦዲት ፊርም የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል።

  1. የኦዲተርነት የሙያ ማረጋገጫ ያላቸው፤
  2. የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
  4. የዘመኑን ግብር ስለ መክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ከፌዴራል ወይም ከክልል የኦዲት መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ ሰነዶችንና የምትሰሩበትን ዋጋ የያዘ ሰነድ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገለፃለን፡፡

አድራሻ፡- ጅግጅጋ ከተማ፣ ጎማጣ መንገድ፣ ረማስ ሆቴል አጠገብ ጅግጅጋ

ለበለጠ መረጃ ስስ ቁጥር: +251-9-15-10-02-31/

ኢሜይል፡- abduilahugas@gmail.com

 

ኦጋዴን እርዳታና ልማት ድርጅት

Save Tender