የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር መክፈላቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ TIN / መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግን/አስ/ደ/ስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ
- ማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ ከሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ የብር /30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር CPO በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ስም አስርቶ ማቅረብ ይኖርበታል
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውሉን ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ ከሚገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ በመሙላት ዋናው (ኦርጅናል! እና ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስም እና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስም እና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ
- ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ለውድድሩ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርበው ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክመንት ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ አለበት።
- ተጫራቾች ከጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO [ጨምሮ ማንኛውም መረጃዎች ለውድድር ከሚያቀርቡት ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በተከታታይ 15 ቀን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል።ጨረታ የሚከፈትበት እለት በአል ወይንም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል
- አሸናፊው ውል ተፈራርሞ ካጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጁ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል ታክስ ያካተተ ወይም ያላካተተ ዋጋ ቫትን ያካተተ ተብሎ ይወሰዳል
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ሁኔታ ቫትን የተጨማሪ እሴት መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።ይህ ካልተገለፀ የቀረበው
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በሊቁጥር 011 365 8463 ወይንም 011 330 1624 ይደውሉ
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ
