ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የመለያ ቁጥር፡- 01/2018 ዓ.ም
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከህጋዊ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- ሎት 1 - የደንብ ልብስ፡- 30,000
- ሎት 2 - አላቂ የፅዳት ዕቃ:- 20,000
- ሎት 3 - አላቂ የቢሮ እቃ፡-10,000
- ሎት 4 - ኮምፒውተር ፎቶ ኮፒና ጥገና፡- 5,000
- ሎት 5 - ህትመት ባነር 1,000
- ሎት 6 - አላቂ የትምህርት ዕቃ:- 10,000
- ሎት 7 - አላቂ ህክምና እቃዎች :- 3,000
- ሎት 8 - የደንብ ልብስ ማሰፊያ- 1,000
- ሎት 9 - ፕላንትና ማሽነሪ መሳሪያ መግዣ:- 30,000
- ሎት 10 - ልዩ ልዩ መሳሪያዎች:- 5,000
- ሎት 11 – ለህንጻና ለቁሳቁስ እና ተገጣጠሚዎች እድሣትና ኮንክሬትናሊሽ 10,000
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO) ካሽ ሪሴስተር ተመዘጋብ የሆኑ / ያለው ብቻ ነው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበት እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ አርጅናል ሰነድና ኮፒ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 02 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በዓየር ላይ ክፍት ሆኖ የሚቆየው 10 (በአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከት/ቤቱ ከገዙት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ሞልተው ከላይ በተራ ቁጥር አራት በተገለፀው መሰረት ጨረታው በአየር ላይ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በስራ ሰዓት በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በተዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥኑ በዓስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን የተጠቀሰውን ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ በዋለ 11 በአስራ አንደኛው / ቀን በጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች የግዥ መጠየቂያ (purchase order) ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ እቃውን የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚጠይቁ እቃዎች ናሙና ማቅረብ እና ናሙና ለመቅረብ የሚያስቸግሩ እቃዎችን በፎቶ ግራፍና በዝርዝር መግለጫዎችን በማያያዝ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተሞላው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማስያዣ ሲፒአ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ባቀረበው ዕቃ ውሉ ሳይቀየር ከተጫራች ጋር በመስማማት እስከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር- 011-8-93-16-37/ 011-8-93-16-37 ወይም በአካል በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በመምጣት ፋይናንስና ግዥ ንብረት አስረዳደር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
የአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
