Tender Detail

Tender Details

  • Company የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን
  • Address ቀበሌ 13 ኢሚግሬሽን ጎን አፈሯ እናት ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ፡ ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-19-99
  • Website
  • Deadline03 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2025-11-03 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Vehicle (Garage Service)

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥዎች (የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥዎች (የኮምፒውተርና የፕሪንተር ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡
  6. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከፎቶ ኮፒና ከኦሪጅናል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ አርዕስት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ቢድ ቦንድ /በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሰርቲፋይድ ቼክ CPO/ ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ ቀርበው በመውሰድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚሸጡበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒውን በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን በኮሚቴ መከፈት እያግደውም፡፡ የሚከበሩ የህዝብ በዓላት ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ጽ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

ቀበሌ 13 አዲስ ካስገነባው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4

ስልክ ቁጥር:- 058-2-22-19-99/058-2-20-19-70

 

የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን

 

Save Tender