Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ አዎት ሶርስ እና የመኪና ኪራይ (ጭነት) የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የኦክሲጅን እና የመድሃኒት የመኪና ጭነት አገልግሎት፣ የጥበቃ እና ደህንነት ስራ፣ የአትክልተኛ እና የጉልበት ስራ፣ አጠቃላይ የፅዳት ስራ፣ የህሙማን አልባሳት እጥበት ስራ (ላውንደሪ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ አዎት ሶርስ እና የመኪና ኪራይ (ጭነት) የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት፣ የኦክሲጅን እና የመድሃኒት የመኪና ጭነት አገልግሎት፣ የጥበቃ እና ደህንነት ስራ፣ የአትክልተኛ እና የጉልበት ስራ፣ አጠቃላይ የፅዳት ስራ፣ የህሙማን አልባሳት እጥበት ስራ (ላውንደሪ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ጨረታውን ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታ ከመክፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታል ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ ፋይናንስ በቢሮ ቁጥር 44 የስራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ። ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያው ይታሸጋል ወዲያው 4፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 09-13-00-54-80 /09-13-03-41-13 /09-13-02-35-71 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ05 / አምስት/ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  9. የመክፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ማንኛውም በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁት ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው፡፡
  11. በወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ከግቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው፡፡
  13. ውድድሩ የምናወዳድረው በጥቅል ነው፡፡
  14. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender