Tender Detail

Tender Details

  • Company Busa Gonofa Oromia (የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ)
  • Address ሳሪስ አዲስ ጎማ /ሆራይዘን/ ፋብሪካ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251114709028
  • Website
  • Deadline03 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security300,000.00
  • opening date2025-11-03 00:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በአዳማ እና በሻሸመኔ ከተማ መጋዘን ውስጥ ስንዴ ለመሸጥ 9,399 ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

Busa Gonofa Oromia (የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ)


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

ስንዴ ለመሸጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ በአዳማ እና በሻሸመኔ ከተማ መጋዘን ውስጥ ስንዴ ለመሸጥ 9,399 ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያማሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

1. ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፤የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ እና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፤

2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዘር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማስረጃ፤

4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትርበሥራ ሰዓት ብቻ የጨረታ ሰነዶቹን ዋናና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 20 ብር 200 በማምጣት ማስገባት አለባቸው ::

5. ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታውን የመክፈት  ሥርዓት ይከናወናል፤

6. ማንኛውም ተጫራች ያልተገደበ የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ የጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ 300,000(ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል፤ እንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

7. አሸናፊዎች እንደተገለጸላቸው ውሉን ለመፈረም የሚያስችል መልካም ሥራ አፈጻጸም ወይም የውል ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ተጫራቾች ጨረታውን ስለማሸነፉ ጠቅላላ ዋጋ 10% በመቶ ዋስትና CPO ወይም በባንከ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በኢንቨሎፕ ዋና እና ቅጂውን ለየብቻ አሽገው የድርጅታቸውን ሙሉ አድራሻ መግለጽ ይኖርባቸዋል፤

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 251114427770 በመደወል መጠየቅ ይቻላሉ፡፡

አድራሻ፡- ሳሪስ አዲስ ጎማ/ሆራይዘን/ፋብሪካ ፊት ለፊት

ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ /ፊንፌኔ/

Save Tender