ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ የተባለ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበር በኢብሳስ የሂሳብ ስታንዳርድ /APSAS Standard/ መሰረት የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ህጋዊ እውቅና ባላቸው አዲተሮች ማስመርመር /አዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
EMBRACING HOPE ETHIOPIA (ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ)
የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ
ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ የተባለ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበር በኢብሳስ የሂሳብ ስታንዳርድ /APSAS Standard/ መሰረት የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ህጋዊ እውቅና ባላቸው አዲተሮች ማስመርመር /አዲት ማስደረግ እንፈልጋለን፡፡ ስለሆነም እ.ኤ.አ ከጥር 01, 2025 እስከ ታህሳስ 31/2025 ያለውን የአንድ አመት የሂሳብ እንቅስቃሴ ማስመርመር እንፈልጋለን፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰአት በድርጅቱ ቢሮ ን/ስ/ላ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 መካኒሳ ቆሬ አካባቢ በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የፋይናንስ እና የኦዲት ሙያ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋ ታክስን ጨምሮ እና የሂሳብ ምርመራውን የሚጠናቀቁበት ጊዜ በመግለፅ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማመልከቻ በተጠናቀቀበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር፡- 0922-5183-97 ወይም 0921-92-34-76
ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ
