የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት4 የፅዳት እቃ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 6 ቋሚ የቢሮ እቃ፣ ሎት 7 መስተንግዶ እና HIV ሚኒስትሪሚንግ ለ2018 በጀት አመት በአዲስ ዘመን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -ግ/ፋ/ን/አስ/ 361 2018
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት4 የፅዳት እቃ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 6 ቋሚ የቢሮ እቃ፣ ሎት 7 መስተንግዶ እና HIV ሚኒስትሪሚንግ ለ2018 በጀት አመት በአዲስ ዘመን ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በዚህም መሰረት፦
-
ተጫራቾች ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲንነበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለባቸው፡፡
-
በተጨማሪ እሴት ታከስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው፡፡
-
ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚሞሉት ዋጋ ከ200 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
-
ተጫራቾች የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒዎችን በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከ 04/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 28/02/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የተዘጋጀውን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመከፈል ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
-
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን⁄ አስ/ ቢሮ ቁጥር 14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 29/02/2018 ዓ/ም በማስገባት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
-
ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
-
የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት የተቆረጠ ህጋዊ ደረሠኝ ማስያዝ የሚገባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ ከሆነ የቆይታ ጊዜው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን መቻል ይኖርበታል፡፡
-
የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
-
አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውስድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
-
ሁሉም የጨረታ ስነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
-
መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው ዕቃ ወይም ገንዘብ ላይ 30% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ተጫራቾች የአማራ ክልል ገ/ኢ/ት/ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
-
አሸናፊው ድርጅት በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ የመንግስትን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ካገኘው በተናጠልም የምናወዳድ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
-
አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚያቀርበው ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ (ኦሪጅናል) ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
-
ለተጨማሪ መረጃ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት በስ/ቁ 033-551-29-61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
