በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር 003/2018
- በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የተለያዩ ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (Tin Number) ያለው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበት መረጃ እና የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርብ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻለው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- ተጫቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሁሉንም መጫረት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስም አሰርተው በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ኮምቦልቻ በሚገኘው በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 551 0205, 033 551 3002, 033 551 2268 ማግኘት ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
