በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት በ2018 በጀት ዓመት፡- ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያ/ስቴሽነሪ/ ሎት-2 ጎማ ሎት-3 ኤሌክትሮኒከስ ሎት-4 ፈርኒቸር 1 ሎት 5 ሁለት እግር ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት በ2018 በጀት ዓመት፡-
ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያ/ስቴሽነሪ/
ሎት-2 ጎማ
ሎት-3 ኤሌክትሮኒከስ
ሎት-4 ፈርኒቸር 1
ሎት 5 ሁለት እግር ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
-
የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈሉ፣
-
በመስኩ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
-
የጨረታ ዋስትና ከሎተ-ı እስከ በሎት-5 10000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ከዳሎቻ ከተማ አሰተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 500/አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ ሰነዱን ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት 6፡00 ሰዓት ድረስ በስልጤ ዞን ከዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-14 በዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ ሳጥኑ ሰነድ ማስገቢያው የጊዜ ሰሌዳ በተጠናቀቀበት እለት ከቀኑ በ6:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0924727270
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የዳሎቻ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
