Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የሚወገዱ ብረታ ብረቶች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የግብርና የእርሻ መሳሪያዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (የመኪናና የሞተር ጎማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የሚወገዱ ብረታ ብረቶች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የግብርና የእርሻ መሳሪያዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (የመኪናና የሞተር ጎማዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፍራሽና ብርድ ልብስ፣ የሚገዙና የሚሰሩ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማ፣ የአንድ አመት የመኪና ጥገና ግዥ የአንድ አመት የመኪና መለዋወጫ እቃዎች አቅርቦት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ የሚወገዱ ንብረቶች 2% ፣ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ የመኪና እና የሞተር ጎማ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/፣ ፈርኒቸር 10,000 /አስር ሺህ/፣ የግንባታ እቃዎች ብር 10,000 /አስር ሺህ/፣ ፍራሽና ብርድ ልብስ 5,000 /አምስት ሺህ/፣ የመኪና መለዋወጫ 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/፤ የመኪና ጥገና 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፤
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ለግ/ንብ/አስ/ቡድን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፣

 

አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ፣

 

በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender