Tender Detail

Tender Details


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ሀይል ለሚገነባቸው የድልድይ ግንባታ ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ብረት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ማ/ስ/መ/ባ/ብረ/04/18

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በራስ ሀይል ለሚገነባቸው የድልድይ ግንባታ ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የግንባታ ብረት ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም አገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ዋና እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን አንድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብቻ በመክፈል በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ገቢ የሚያደርጉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያው ቀን 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ (CPO) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) ብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም

ስልከ ቁጥር፡- 0113659932

ወልቂጤ/ኢትዮጵያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን

 

Save Tender