Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድበ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/02/2018

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት አመት የተጠቃለለ ግዥ ከዚህ በታች በተቀመጡት የጨረታ ሰነድ የሎት ምድበ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

  • ሎት-1 የጽህፈት መሳሪያ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሃሳብ መስጫ ሰማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም።
  6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመቀበያ ደረሰኝ በአ/ፉ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በምርጫቸው በእንዱ ከዋና /orgina የመወዳደርያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል።
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት በአፉ ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የሕዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የሥራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሠዓት የንግድ ፈቃድና ሁሉንም ማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናሉንና የማይመለስ አንድ አንድ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት አለባቸው።
  14. መ/ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በሎትም ሆነ በተናጠል አማራጩን ይዞ በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ብቻ ሲሆን ከሚፈለጉት እቃዎች መካከል ለከፊሎቹ ብቻ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፡፡
  15. መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0334490061 ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻችን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብ/ዞን የአርጡማ ፉርስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender