Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251462120120
  • Website
  • Deadline21 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price250.00
  • Bid Security25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-21 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያ (ዕቃዎችን) እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

Hawassa University College of Medicine and Health Sciences (የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር- HU/CSH/NCB/የፅዳት ዕቃዎች/01/01/2018 BY HU/CSH/NCB/የጽህፈት መሳሪያ/02/02/2018 BY

HU/CSH/NCB/ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች/03/03/2017 BY

 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፅዳት ዕቃዎችን፣ የጽህፈት መሳሪያ (ዕቃዎችን) እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ለማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ ድረ-ገጽ /web-site/ ላይ የተመዘገበ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለእያንዳንዳቸው ጨረታ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም እና ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ግዥ ሥራ አስፈጻሚ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. የጽዳት ዕቃዎች እና የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ጨረታዎች ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡40 ሰዓት ላይ፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡40 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር፡- +251-4-62-12-01-20

ፋክስ ቁጥር- +251-4-62-20-87-55

 

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

 

Save Tender