ፔቭ ሎጀስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Pave Logistics Inspiring Business Precision (ፔቭ ሎጀስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
ልዩ ልዩ ንብረቶች የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ፔቭ ሎጀስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታ የሚወዳደሩት ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ቃሊቲ ጣና ቁፋሮ ሳይደርስ 500 ሜትር በስተቀኝ ወረድ ብሎ በሚገኘው ድርጅታችን ከፍለው ጋራዥ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በፔቭ ሎጂስቲክስ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሽገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ፔቭ ሎጂስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃየተ/የግ/ማህበር ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ከመስከረም 25/2018 እስክ ጥቅምት 12/2018 ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ከላይ በተጠቀሰው መስሪያ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፔቭ ሎጀስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድርጅታችን ጋራጅ አገልግሎት መሰብሰቢያ ቦታ ይከፈታል ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ፍቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አስተጓጉለውም።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በዋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ሰነድ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0111262622 ወይም በ0923940237 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ድርጅቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ፔቭ ሎጀስቲክስ እና ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
አዲስ አበባ
